” ምን ነበረ መልሱ? ” (ሻቪን ሚራ)

ምን ነበረ መልሱ? ” (ሻቪን ሚራ)


ምን ነካው ይህ ልቤ ሸሽቶኝ እየራቀ
ለኔ ባልሁት ነፍስ ውስጥ አንችን አፀደቀ
ስምሽን ሲጠሩ ስሜ እየመሰለኝ
ምን ነካው ልሳኔ አቤት የሚልብኝ
ምስልሽን እያየ በነጋ በጠባ
ምን ነካው ይሄ አይኔ ዥረት የሚያነባ
በአንድ የፁሁፍ መልዕክት መሳምሽን ስትነግሪኝ
ምን ነካው ከንፈሬ ደርቆ የነበረው የሚለሰልሰኝ
ለምን ይሆን ውዴ ከአንች ጋራ ስሆን ቀኑ እያጠረብኝ
የቀጠርሁሽ እለት እየተከመረ ዳገት ሚሆንብኝ
በአንችነትሽ ገዳም ከነነፍሴ ሞቼ
ያልሽኝን የምሆን ማንነቴን ትቼ
ምን ነካው ኩራቴ የወንድነት ወጉ
ባንዴ ተልፈስፍሶ እንዲህ መጠውለጉ
ምንድን ነው ያደረገሽኝ ንገሪኝ በሞቴ
ከአለት የጠጠረው የት ሄደ እኔነቴ?

Leave a Comment