ርስት ለባለቤቱ (ሊዲያ ዘጊዮን አማራ)

ርስት ለባለቤቱ (ሊዲያ ዘጊዮን አማራ)

በእውነቱ ከሆነ እስከ አሁን ወያኔ በአደገኛ ሁኔታ machiavellianism style ተጥቅማ ፖለቲካውን ለማጣጠፍና በፖለቲካ ምህዳር የበላይነትን መያዝ ችላ ነበር:: ነበር። ነገር ግን የሾመችው ሰው ስልጣን በያዘ በ፩፫ኛ ቀን ላይ ካርዷን በሙሉ አቃጥሎ ጨርሶባታል፤ ይሄንን የደረሰባቸውን ያልታሰበና ያልተገመተ ነው ብል የምሳሳት አይመስለኝም። በተናገረ ቁጥር አየፎረሸባቸው ተቸግረው የድህረገጽ ጸሀፍቶቻቸው በdamage control ስራ ላይ ተጠምደው ይስተዋላሉ።

ወያኔ ችግር ውስጥ ገብታለች። ይሄኛውን ማእበል እንደማትሻገረው በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል፤ የወልቃይትን ጉዳይ አለመዳሰስ ብልጠት ነበር:: ከዳሰሱም ደግሞ ህጉ በሚያዘው መሰረት ዳግም ከፍተን እናየዋለን በማለት ግዜ መግዛት ሲችሉ የሞተር ጠባያቸው እልከኝነት እስካሁን ተክነውት በመሪነት ከተወኑት ፖለቲካ ምጥቀት ጫፍ በፍጥነት አየተወረወሩ የመፈጥፈጥ ጉዞዋቸውን ላየ አስፈሪ ላይቭ ፊልም ሆኗል። በዚህ አደንዛዥ በመሰለው ሶፖፕራ ህዝበ አዳሙን አደንዝዘውት ቆይተው ባልተጠበቀ አጋጣሚ በታመኑበትና የሾሙት የፊልም ተዋናይ ፊልሙን በፍጥነት ወደ አስፈሪ (Horror movie) ፊልምነት ሲቀይርባቸው የከተታቸው የፖለቲካ ክስረት በትንሹም ስርዐቱን እየደጎሙ በነበሩ የውጭ ሀይሎች ሳይቀር ትልቅ ፍራስትሬሽን እንደሚፈጥር ለመገመት ነብይነት አያሻውም። ካሻውም ነብይ በሽ ነው ዘንድሮ ጠጋ በል አንድ ቸርች ይተነትንልሀል:: የዛሬ ስድስ አመት ግን ሲተነበይ ለአቦይ ኣብይ የስንት ቀን ስልጣን ተብሎ ነበር?

ኣቦይ ኣብይ ትልቅ ኪሳራ ሆነዋል ለወያኔ። የሀይለማርያም ያለህ አስኪል ህዝበ አዳም የሰውየው ግልብነት እና የእውቀት ማነስ ታይቷል፤ ጮሌነታቸው አጋሮን አያሳልፍም። ኣቦይ ኣብይ ወይ የዳበረ በእውቀት የተቃኘ ንግግር ወይን በበሰለ ጮሌነት መገለጥ አቅቷቸው ተስተውለዋል። በጋዜጣዊ መግለጫ ንግግራቸው ያናናቁት ፈስቡክ ላይ እንኳ በጦማሪነት አንድ ተከታይ አያፈሩበም እስካሁን በተናገሩት ነገሩ ሲመዘን ሌላው ይቅርና።

በቦንብ ላይ መረማመድ ይቀር ብለን ነበር፣ እነሆ ወያኒት ሆይ ቦንቡ መፈነዳዳት ጀመርልሽ፤ አሁን የወልቃይት ጉዳይ ወደ ገደለው ይገባል ማለት ነው። ያ ደግሞ ወልቃይት፣ ሰቲት ሁመራ፣ ጠለምት፣ አርማጭሆ፣ ራያ፣ መተከል፣ ሸዋን አስመልሶ ብቻ የሚመለስ አይሆንም:: ስልጣነ መንበሩን ነቅንቆና ገርስሶ ብሎም ወያኔን ለፍርድ የሚያቀርብ ይሆናል፤ ሸሽታችሁ ሌላም አገራት ላይ እንዳትሰየሙ SRes ፩፮፰ የተዘረፈ ገንዘብ በየትኛውም የውጭ ባንክ አንዲቀዘቅዝ ያደረጋል ማለት ነው፤ አሁን ሁለት ምርጫ አለ።

አንደኛው የአማራውን ርስት በሙሉ መልሶ ትንሽ ቢሆንም ግዜ በመግዛት መቀመጥ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ወልቃይትንና መሰል አማራ ክልሎች የሙጥኝ በማለት ሞትንና ወርደትን ማፋጠን ይሆናል። ምርጫው በእጃችሁ ነው። ግዜን ምስክሩ አድርጎ የተጠመደው ቦንብ እየቆጠረ ነው። ፈንድቶ ድብልቅልቁ ከመውጣቱ በፊት ግዜ ብትገዙ ለራሳችሁ ትመከራላችሁ። ከመሞት መሰንበት እንዲል አማራ የሰው ንብረት መልሱና ሰንብቱ፤ ተመከሩ። በስትእርጅና ሮጠው ላለማምለጥ ምን ያላልጣል?

የኣቦይ ኣብይ የጫጉላ ሽርሽር ቃና ያጣ ንግግር ባታስደግሙት ለራሳችሁ ነው ጥቅሙ። ታሪካችሁ አንዳይሆን ይሆናልና። ምን ታሪክ አለንና በሚል እብሪት ከመተጣችሁም እንዳሻችሁ። ዳሩ ምን ታሪክ አላችሁ ተበላሸ ኖረ?!

የአማራነት የህልውና ጥያቄ ይከበር!

 

ሊዲያ ዘውዱ (ሊዲያ ዘጊዮን አማራ)

Leave a Comment