ሰላማዊ ሰውን የመግደል ሱስ የተጠናወተው አግዓዚና የሞያሌ የማክሰኞ ውሎ | ከሞያሌ ሸሽተው ኬኒያ የገቡ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር ከ30ሺህ በላይ ደርሷል፡፡ (ወንድወሰን ተክሉ)

ሰላማዊ ሰውን የመግደል ሱስ የተጠናወተው አግዓዚና የሞያሌ የማክሰኞ ውሎ | ከሞያሌ ሸሽተው ኬኒያ የገቡ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር ከ30ሺህ በላይ ደርሷል፡፡ (ወንድወሰን ተክሉ)

እሁድ እለትም በተመሳሳይ ስህተት የህወሃቱ ገዳይ ሰራዊት አንድን ሰው በአስር ጥይት ወንፊት አድርገው ገድለዋል፡፡

በእለተ ቅዳሜ የንጹሃንን ደም በሞያሌዋ ሸዋ በር በግፍ ያፈሰሰው አግዓዚ ሰኞ ማት ከምሽቱ አራት ሰዓት ላይ በመነሃሪያ አካባቢ ከባድ ጥቃት እንደተፈጸመበት የሞያሌ ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡

ጥቃቱ ዛሬ ማክሰኞም ቀጥሎ በርካታ የመከላከያ ሰራዊት ክሞያሌ አስርና አስር አምስት ኪሎ ሜትር እርቃት ላይ ሙትና ቁስለኛ እንደሆነ ነግረውኛል፡፡

ሞያሌ በከፍተኛ ውጥረት ላይ ትገኛለች፡፡
ዛሬ ማክሰኞ ታጣቂ ሽፍታ ለማጥቃት የዘመተ አንድ ሙሉ ኦራል ሰራዊት እንደተመታ ገልጸውልኛል፡፡

መከላከያው ከፊቱ የአካባቢውን ታጣቂ ሚሊሺያ በሁለተኛ ረድፍ ላይ የኦሮሚያን ፖሊስ ካሰለፈ በሃላ እራሱን በሶሰተኛ ረድፍ ከሃላ አሰልፎ ለዘመቻ የተሰማራ ቢሆንም ታጣቂዎቹ የመጀመሪያዎቹን ሁለት ረድፍ ሰልፈኞችን በማለፍ መከላከያውን ቆርጠው እንደደመሰሱት ገልጸዋል፡፡

እንደ የሞያሌ ነዋሪዎች ገለጻ በአካባቢው ሚሊሺያ፤በኦሮሚያ ፖሊስ ሃይልና በአማጺው ታጣቂ ሃይል መካከል መልካም የሆነ መናበብና መተባበር ተፈጥራል ብለዋል፡፡

በመላው ዓለም የመከላከያ ሰራዊት ሃይል በስህተት ንጹሃንን ሲገድል መስማትም ሆነ ማየት አዲስ ነገር አይደለም፡፡ ግን የሚፈጸመው የስህተት ትቃት የኢትዮጵያውን ለየት ያለና አዲስ ያደርገዋል፡፡ በጦርነት ቀጠና ውስጥ መከላከያ በአየር ሃይልና በከባድ መሳሪያ ድብደባ ኢላማውን በመሳት ያልታጠቁ ንጹሃንን ሲደመሥስ ቢሰማም የኢትዮጵያው ግን ጦርነት በማይካሄድበት የሰላም ቀጠና ያውም በሰላማዊ ከተማ የጭፍን ጅምላ ጭፍጨፋን ከዓለም ሁሉ በተለየ ሁኔታ በስህተት የተፈጸመ እንዳይባል ያደርገዋል፡፡

በሰላማዊ ህዝብ ውስጥ የሚሰማራ መከላከያ ሰራዊት ከተሰማራበት ሲቪል ማህበረሰብ ትእግስት አስጨራሽ ትንኮሳና ጥቃት ሲፈጸምበት አፈሙዙን ባለማዞር የሚታወቅ ቢሆንም የኢትዮጵያው ግን አይደለም እየተጠቃ ዝም ለማለት ይቅርና ምንም ሳይጠቃ ንጹሃንን እራሱ ተተናኩሶ መልሶ በጅምላ ሲጨፍጭፍ ደግሞ ተደጋግሞ ታይቷል፤ ወደፊትም ሲፈጸም ይታያል፡፡

ለምንድነው ይህ ሰራዊት ርህራሄ አልባ የሆነው ?

ለምንድነው ይህ ሰራዊት ወገኖቹን በመግደል ሱስ የተጠመደው ?

***የመከላከያ ሰራዊቱ የተጠናወተው ንጹሃንን የመግደል አደገኛ ሱስና መንስኤው

ከዓመታት በፊት-ያ-አንድ ቋንቋ፣አንድ ሃይማኖትና አንድ ነገድ ሆነው ግን መግባባት ባለመቻል እርሰበርስ ሲባሉና ሲጫረሱ ሀገራቸውን መንግስት አልባ ያደረጉት ሶማሊያዊያን መንፈስ የሀገሬ እምዬን ምድር ተቆጣጠረ እንዴ እያልኩ እራሴን በጥያቄ እንዳስጨንቅ ያስገደደኝ የሀገራችን ሁኔታ አንድ ያላስተዋልነው ከበድ ያለ ነገር መኖሩ ይሰማኛል፡፡

የ «መከላከያ» የተባለው ወታደር ገዳይ መንፈስ እጅግ ያላስተዋልነውና ትኩረትም ያልሰጠንበት ባእድ ክስተት ጉዳይ አሁን አሁን እረፍት ነሺ ሆኖብኛል፡፡

ወታደሩ በመግደል ሱስ ተመርዟል፡፡ ያ ደግሞ በመላው ዓለም ያለ የማንኛውም ወታደር ስነ ባህሪ ነው ብዬ ውስጣዊ ጩህቴን አደብ እንዳላስገዛ ስውን መግደል በትምህርትና በስልጠና መልክ የተማረው መከላከያ ጦር ሁሉ በሰው ገዳይነቱ የታወቀ ቢሆንም የሚገድለውን ግን ለይቶ የሚያውቅ ነውና ከሀገራችን ወታደሮች እርምጃ ጋር አታመሳስል ይለኝና ድርጊታቸው እተወዋለሁ፡፡

የህወሃት መከላከያ ሰራዊት ሶማሊያዊያኑን የተጠናወተው ገዳይ መንፈስ የተጠናወተው ይመስል ጠላትን መግደል እጅግ ተጠይፎ ንጹሃንን መፍጀቱን ያለመሸማቀቅ ተያይዞታል፡፡

ጥፋተኛ ሆኖ መገኘትም ለግድያ የሚያበቁ ክስተቶች አይደሉም ለዚህ የህወሃት ወታደር፡፡

ይህ በመጠሪያ ስሙ አግዓዚ ግን በቅጽል ስሙ ናዚ ተብሎ የሚጠራው ተዋጊ ክፍል ተታኩሶና ተዋግቶ ጠላት የተባለን ሃይልና ተዋጊን ከመግደል ይልቅ ያልታጠቀ፣መልሶ ሊተኩስበት የማይችልን ሰላማዊ ሲቪል ሰው መግደል ያመረቅነዋል ሲሉ የገዳዩ አባል የነበሩና በአንድ ወቅት አጫውተውኝ ያጣጣልኩት ታሪክ እውነተኛነት ይታየኝ ጀምራል፡፡

የአጸፋ መልስ መስጠት የማይችልን ሰው መግደል ይህን ተዋጊ ክፍል ክፉኛ አመርቅኖና አደንዝዞ በእርካታ አየር ላይ ያራምደዋል ሲሉ አባል የነበሩ ነግረውኛል፡፡

ምን ማለት ነው? ብለን አባባሉን መጠየቅና መጠርጠር ቀርቶ ልንንቀውና የተናጋሪውንም ንቃተ ግንዛቤ እሚዛን ላይ ልናስቀምጥ እንችል ይሆናል፡፡
ግን ይህንን ታሪክ የሰራዊቱ አባላትና በሶማሊያ ተሳታፊ (በአሚሶም ስር) በሚገባ ይናገራሉ፡፡

መሳሪያ መዝዞ የተታኮሰን ወታደር ከመግደል ይልቅ በፍርሃት ተወርሮ ወይም ህግ አክባሪ ነኝ ብሎ ከቤት ጋዳው የተቀመጠን ሰው መግደል እጅግ እንደሚያመረቅናቸው ደጋግሞ ሲወራ ሰምቻለሁ፡፡

ለመሆኑ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በእነዚህ ወታደሮች የተገደሉ ኢትዮጵያዊያንን ሁኔታ በአግባቡ ትኩረት ሰጥተን ተከታትለናልን?

የቅርቡን እስቲ እንየው፡ በሞያሌ፤ በጉደር፤በጨለንቆ፤በወልዲያ፤በመንዲ፣በጎንደር ወዘተ የሞቱ ሰዎችን ታሪክ ልብ ብለን ካስተዋልን ህወሃት በሞያሌው ጭፍጨፋ ብቻ የይስሙላ ስህተት ነው ጩህቷን ከማሰማት በስተቀር በአንዱም ግድያ ላይ የተነፈሰችው ቃል የለም፡፡

ግድያዎቹ ሁሉ ማለት ባይቻልም አብላጫዎቹ በገዳይ ወታደሩ ሆን ተብሎ ምንም ያላጠፋን ንጹህ ዜጋን መግደል እንዳለበት አምኖበት ለእርካታው ሲል የወሰዳቸው እርምጃዎች እንደሆኑ ታሪኩ ይመስከራል፡፡

ይህ የመግደል ሱስ የተጠናወተው ወታደር ማንኛውንም ሰው ለመግደል የሚያበቃ ምክንያትን አያጣም ይላሉ፤ አባላቱ፡፡

ከተቀረውም ስራዊት በተለየ ሁኔታ ይሄ ደም ያሰከረው የሚባል አይነት ገዳይ ሰራዊት ቢሆንም አባላቱ ለዚህ የዳረጋቸውን መንስኤ በውል ለይተው አያውቁም፡፡

እርኩስ መንፈሳዊ ስሜት የተቆጣጠራቸው ወይም የሚሰጣቸው ፍርሃት ማደንዘዣ እጽ መድሃኒት እንደሆነ ቢናገሩም እራሳቸውም በግልጽ አልገባቸውም፡፡

እኔንም ሆነ እነሱን የገባቸው አንድ ነገር ቢኖር መንፈሳቸውና አስተሳሰባቸው የማንኛውም ጤናማ ሰው መንፈስና አስተሳሰብ እንዳልሆነ ብቻ ነው፡፡

የመግደል ሱስ ያጠቃው፤ ያውም ጠላቱን ሳይሆን የራሱን ያልታጠቀ ንጽኋንን መግደል ሱስ የተጠመደን ሰራዊት ጥይትና ጥቃት በጨዋነትም ሆነ ከቤት ባለመውጣት የምታመልጠው አለመሆኑን ስትሰማ ከቤቴ በአልጋዬ ከምገደል …ያሰኘሃል፡፡

በፈሪና በጀግና መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው?

ሁለቱም ማቾች ሲሆኑ ጀግናው ለመብቱ፣ለክብሩና ለነጻነቱ እየተዋጋ በፊት ለፊቱ ተናንቆ ሲሞት ፈሪ ደግሞ ለህይወቱ እጅግ በመሳሳት፣በመፍራትና ህይወቱን ለማዳን በመሻት የሃሊት ሽሽት እየሮጠ በጀርባው ተመትቶ ይሞታል፡፡

ፈሪም ሆነ ጀግና ከሞት አይተርፉም፤ ሁለቱም ይሞታሉ ግን የሁለቱም አማማት እጅግ ይለያል፡፡ ማንኛውም ሰው ከሁለት አንዱን መምረጥ ይቻለዋል፡፡

የህወሃት ገዳይ ወታደር በመግደል ሱስ የተጠመዱት በፍርሃት፣በይሉኝታና በግድየለሽነት የተጠመድነውን ሰዎች በቀላሉ መግደል በመቻላቸው ምክንያት ብቻ ሳይሆን እኛም በቀላሉ እጅ አጣጥፈን ጥይታቸውን ስለተቀበልን ሱሰኝነታቸው እየጠነከረ መምጣቱን እገምታለሁ፡፡

እነዚህ ገዳይ ወታደሮች ከገደሉን ይልቅ የእኛ ለእነሱ ምቹ ተገዳይ ኢላማ መሆንን ይበልጥ እንዳስጠቃን እና እያስገደለንም እንዳለ ይታያል:፡

ለምን ለመገደል ተስማማን?

ለምን ለመገደል እንስማማለን?
ባለመገደል ውሳኔያችን ምን ያህል ከገዳዮቻችን ጋር ተናንቀናል?
ጎበዝ እነዚህን የመግደል ሱሰኞችን በመሸሽና በመታዘዝ ህይወታችንን አንታደጋትም፤ በየተራና ስፍራ እየዞሮ የመግደል ሱሳቸውን ለመወጣት መከላከልና ማስቀረት የምንችለው የገዳዮን መግደያ ደም በማፍሰስ ብቻ ነው፡፡
ምርጫውም አንድ ብቻ ነው፤
ከጠላት ጋር ለመብት፣ለነጻነትና ለክብር በክብር እየተዋጉና እየተጋደሉ ማለፍ ወይም እድናለሁ ብሎ ወደ ኋላ በመሸሽ ከጀርባ ተመትቶ መገደል፡፡

ፈሪም ሆነ ጀግና ይሞታሉ፤ አሟሟታቸው ብቻ ይለያል፤ ምርጫውም የእያንዳንዳችን ነው፡፡

ወንድወሰን ተክሉ

Leave a Comment