በአራጣ ማበደር የታሰሩት የአዲስ ቪው ሆቴል ባለቤት ሆቴሉ የአቶ አዲሱ ለገሰ መሆኑን ተናገሩ

በአራጣ ማበደር የታሰሩት የአዲስ ቪው ሆቴል ባለቤት ሆቴሉ የአቶ አዲሱ ለገሰ መሆኑን ተናገሩ
ሃምሌ 13 ቀን 2009 ዓም በአራጣ ማበደርና በሰነድ ማጭበርብር ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት አቶ አብይ አበራ በምርምራ ወቅት ሆቴሉ የእኔ ሳይሆን የአቶ አዲሱ ለገሰ ነው ብለው መናገራቸውን የኢሳት ምንጮች ገለጹ። ማእከላዊ እስር ቤት ውስጥ ታስረው የሚገኙት አቶ አብይ፣ ሆቴሉ የእርሳቸው ሳይሆን በእርሳቸው ስም ያሰሩትና የሚያንቀሳቅሱት አቶ አዲሱ ለገሰ መሆናቸውን ለመርማሪዎች ተናግረዋል።

ፖሊስ ምርመራየን አልጨረስኩም በማለት ሃምሌ 21 ቀን 2009 ዓም ተጨማሪ 14 ቀናት እንዲሰጠው ፍርድ ቤቱን ጠይቆ 12 ቀናት የምርመራ ጊዜ ተፈቅዶለታል። ፖሊስ ግለሰቡ ሃብቱን ያፈሩት ከ1997 ዓም ወዲህ መሆኑን ለፍርድ ቤቱ በመግለጽ፣ በእርሳቸው ስም ያሉትን ንብረቶች አሳግዷል።


ፍርድ ቤት በጠበቆቻቸው አማካኝነት የቀረበውን የዋስትና ጥያቄም ውድቅ አድርጎታል። ፖሊስ በብአዴኑ መስራችና ነባር ታጋይ በአቶ አዲሱ ላይ ምርመራ ይጀምር አይጀምር የታወቀ ነገር የለም። አቶ አዲሱ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከፍተኛ ገንዘብ በሚያንቀሳ ባለሃብቶች ስም በባህርዳር እና በአዲስ አበባ የተለያዩ የንግድ ድርጅቶችን መክፈታቸውን ምንጮች ይገልጻሉ።

ምንጭ ፡ ኢሳት

Leave a Comment