ኢሕአዴግ ምን እንዲሆን ነው የሚፈልጉት? (በፍቃዱ ሃይሉ)

(ጨዋታ ነው። ቀላል ቁምነገር አዘል ጫወታ። ለሚከተሉት ጥያቄዎች የራስዎን መልስ ይስጡ። ለጥያቄዎቹ ከሚመርጡት መልስ ፊት በቅንፍ የተቀመጠውን ነጥብ ይመዝግቡ።)
1) ኢሕአዴግ ቢወድቅ አገሪቱ ትበታተናለች?
☞ በፍፁም (6)
☞ ያስፈራኛል (4)
☞ ያለጥርጥር (2)
2) ኢሕአዴግ በሕጋዊ መንገድ ሥልጣን የያዘ እና ሕዝባዊ ቅቡልነት ያለው ፓርቲ ነው?
☞ ኧረ በጭራሽ (6)
☞ በከፊል፣ አዎ (3)
☞ እንዴታ (1)
3) የፀጥታ ኃይሎች ስለሚያደርጉት የሰብኣዊ መብት ጥሰት ፓርቲው/መንግሥት በቂ መረጃ እያለው፣ ለፖለቲካ ትርፍ ሲባል በይሁንታ የሚያልፈው ነው።
☞ ፈላጭ ቆራጩ ማን ሆነና? (6)
☞ በከፊል እውነት፣ በከፊል ግ:ነት ነው (4)
☞ የጠላት ሐሜት ነው (2)
4) ኢሕአዴግ የሚያጠፋው ጥፋት ለልማት በሚያደርገው ጥረት እንጂ በክፋት አይደለም።
☞ ኧረ ቀናነት ሲያልፍም አይነካካው (3)
☞ አንዳንዴ፣ አዎ (2)
☞ ልክ ነው (1)
5) በኢትዮጵያ ያለው አምባገነናዊ ስርዓት እና ቢሮክራሲያዊ አሠራር መሪዎቹ ሳይቀየሩ የመለወጥ ዕድል አለው?
☞ በፍፁም (6)
☞ ይመስለኛል (3)
☞ ያለጥርጥር (1)
6) የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ከኢሕአዴግ የበለጠ አምባገነን ናቸው።
☞ ውሸት (3)
☞ ትንሽ ቢጋነንም እውነት ነው (2)
☞ እውነት (1)
7) የኢሕአዴግ መንግሥት ኢትዮጵያውያን ለደረሱበት የሥልጣኔ ደረጃ ይመጥናል?
☞ በፍፁም (6)
☞ በከፊል (4)
☞ አዎ (2)
8) ባለፉት 10 ዓመታት ኢትዮጵያ አመርቂ የኢኮኖሚ ዕድገት አሳይታለች ወይስ አላሳየችም?
☞ አላሳየችም (6)
☞ ችግሩ ፍትሓዊ የሀብት ክፍፍል የለም (3)
☞ አሳይታለች (1)
9) የነጻ ሚድያ ነጻነት ለማሽቆልቆሉ ተጠያቂው ማነው?
☞ ኢሕአዴግ (3)
☞ ጋዜጠኞችም፣ ገዢው ፓርቲም (2)
☞ የጋዜጠኞች ሥነምግባር ጉድለት (1)
10) በኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኞች ለመብዛታቸው ምክንያቱ ምንድን ነው?
☞ የኢሕአዴግ አምባገነንነት (6)
☞ ፖለቲከኞች ሚዛናዊ አለመሆናቸው (4)
☞ ፖለቲከኝነት ለሽብርተኝነት ሽፋን መሆኑ (2)
(አሁን፣ ለዐሥሩ ጥያቄዎች የሰጡትን መልስ ይደምሩት። ድምሩ 22 እና ከዚያ በታች ከሆነ ኢሕአዴግ *እንዲሁ እንዲቀጥል* ነው የሚፈልጉት። ከ23 እስከ 41 ከሆነ ኢሕአዴግ *እንዲሻሻል* ነው የሚፈልጉት። 42 እና ከዚያ በላይ ከሆነ ደግሞ ኢሕአዴግ *እንዲወርድ* ነው የሚፈልጉት። ራስዎን የት አገኙት?)

Leave a Comment