የአሥራ ሁለት አምባሳደሮች ምደባ ይፋ ሆነ | ከነዚህም መካከል የምርጫ ቦርድ ሃላፊው ፕ/ር መርጋ በቃና ይገኙበታል

ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ ሐምሌ 19 ቀን 2009 ዓ.ም. የሰጡት የአሥራ ሁለት አምባሳደሮች ሹመት ምደባ ይፋ ሆነ:: የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ ጽሕፈት ቤት በፌስቡክ ገጹ ይፋ እንዳደረገው፣ አምባሳደር ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ አቶ ሥዩም መስፍንን ተክተው የቻይና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሆነው ተመድበዋል:: አቶ ካሳ ተክለ ብርሃንም አቶ ግርማ ብሩን ተክተው የአሜሪካ ባለሙሉ ባለሥልጣን አምባሳደር ሆነዋል::

በተመሳሳይ የቀድሞ የሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስትር ወ/ሮ አስቴር ማሞ የካናዳ፣ የቀድሞው የትምህርት ሚኒስትር ሽፈራው ተክለ ማርያም (ዶ/ር) የደቡብ አፍሪካ፣ እንዲሁም የቀድሞ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ የስዊዲን ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሆነው ተመድበዋል::

ከዚህ በተጨማሪ አምባሳደር ተበጀ በርሄ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ፣ አቶ መታሰቢያ ታደሰ የኳታር፣ የቀድሞው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር አድማሱ ፀጋዬ የኢንዶኔዥያ፣ ወ/ሮ ሉሊት ዘውዴ የሩዋንዳ፣ የሥነ ምግባር ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ዓሊ ሱሌይማን የፈረንሣይ፣ እንዲሁም አቶ ሙሉጌታ ዘውዴ የሱዳን ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሆነው ተመድበዋል::

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ ረዳት የነበሩት አቶ እውነቱ ብላታ በብራሰልስ የአውሮፓ ኅብረት አምባሳደር መሆናቸው ታውቋል::

የአሥራ ሁለት አምባሳደሮች ምደባ ይፋ ሆነ | ከነዚህም መካከል የምርጫ ቦርድ ሃላፊው ፕ/ር መርጋ በቃና ይገኙበታል

ሪፖርተር

Leave a Comment