የአውሮፓ ክለቦችን ያካተቱ የዝውውር ዜናዎች


“ከክለብም በላይ” የሚል መርህን ሰንቆ የሚንቀሳቀሰው የካታሎኒያው ክለብ ኩራት ባርሴሎና ብራዚላዊውን ጥበበኛ ኔይማር በመሸጥ ወደ ካዝናቸው ካስገቡት €222M ውስጥ €120M በማውጣት ለሌላኛው ብራዚላዊ የሊቨርፑል አማካይ ፌሊፔ ኩቲንሆ የማዋል ዕቅድ አላቸው እንደ Daily starዘገባ ።

ካታሎኒያኑ ኔይማርን ካጡ በኃላ ትልቅ ስም ያለው ተጨዋች በዚህ የዝውውር መስኮቱ ወደ ካምፕ ኑ ማዘዋወርን ይሻሉ፡፡ እናም ባርሴሎና ጥቂት ቀናቶች በቀሩት በዚህ የዝውውር መስኮቱ ፌሊፔ ኩቲንሆ ሆነኛ እቅዱ አድርጎ እየሰራ ነው የቦሩሲያ ዶርትመንዱ ሙሳ ዴምቤሌም ሳይዘነጋ ማለት ነው፡፡

የአንድ አመት ውል ብቻ የሚቀረው የአርሰናሉ አጥቂ አሌክሲስ ሳንቼዝ በቀጣዩ አመት በኤምሬትስ የመቆየት ፍላጎት የለውም እንደ ሚረር ዘገባ።

ቺሊያዊው ኢንተርናሽናል እስከ 2018 ግንቦት ድረስ የሚያቆይ ኮንትራት በመድፈኞቹ ቤት ቢኖረውም በዚህ የዝውውር መስኮት በተለይ በፔፕ ጋርዲዮላው ማንቸስተር ሲቲ በጥብቅ እንደሚፈለግ ይታወቃል። አርሰን ቬንገር በኤምሬትስ እንዲቆይ ቢጠይቁትም ➐ ቁጥር ለባሹ አጥቂ ግን በቀጣዩ አመት ኮንትራቱ አልቆ በነፃ ወደ ሌላ ክለብ መጓዝን አይሻም፡፡

ሮማ ለሌስተር ሲቲው አልጄሪያዊ ኮከብ ሪያድ ማህሬዝ ገንዘብ ጨምሮ ወደ ኪንግ ፓወር ማንኳኳቱን ተያይዞታል እንደ Sky Sport (via TalkSport) ዘገባ።

የሮም ከተማ ክለብ የሆነው ሮማ ሞሀመድ ሳላህን ለሊቨርፑል ከሸጡ በኃላ የአጥቂ መስመራቸውን ይበልጥ አስተማማኝ ለማድረግ በሌስተር ደስተኛ ያልሆነውን አልጄሪያዊውን ኮከብ ለመውሰድ ቋምጠዋል፡፡ ነገር ግን ከዚህ በፊት ሮማ ያቀረበውን £31M ቀበሮዎቹ ውድቅ ያደረጉ ሲሆን በትንሹ £35M ይፈልጋሉ፡፡

አርሰናል ብራዚላዊውን የፒ.ኤስ.ጂ የክንፍ አጥቂ ሉካስ ሞራ ወደ ኤምሬትስ ለማምጣት ጥረት እያደረገ ነው UOL ዘገባ። የብሄራዊ ቡድን አጋሩ ፓርክ ደ ፕሪንስ መክተሙን ተከትሎ ሉካስ ሞራ በፈረንሳዩ ክለብ የቋሚነት ዕድልን እንደማያገኝ የታወቀ ጉዳይ በመሆኑ ነው። አርሰናል እና አንዳንድ የጣሊያን ክለቦች ልጁ ላይ ፍላጎት ያደረባቸው፡፡

አርሰናል ከዚህ በፊት ለ24 አመቱ ብራዚላዊ የዝውውር ጥያቄ አቅርቦ ውድቅ የሆነበት ቢሆንም አሁን እስከ €31M የሚያቀርብ ከሆነ ግን ፔዤ ልጁን ማሰናበት ይፈልጋል፡፡

የእንግሊዙ ሻምፒዮን ቼልሲ ዌልሳዊውን የሎስብላንኮስ ውድ ተጨዋች ጋሬዝ ቤል ከሳንቲያጎ ቤርናቦ ለማስኮብለል ጠንክሮ በመስራት ላይ ይገኛል እንደ Sunday Express ዘገባ።

ሪያል ማድሪድ የሞናኮውን የ18 አመት ኮከብ ኪሊያን ምባፔ ለማስፈረም መፈለጉን ተከትሎ ዌልሳዊው አልሞ ተኳሽ ነጫጮቹን የመልቀቅ ፍላጎቱ ከፍተኛ ነው፡፡የጆዜ ሞሪንሆ ማንቸስተር ዩናይትድ የረዥም ጊዜ የቤል ፈላጊ ቢሆንም ሰማያዊዎቹ ከፍሎረንቲኖ ፔሬዝ ጋር በመደራደር £90M በማቅረብ ከቀያይ ሰይጣኖቹ መንጋጋ የማውጣት እቅድ አላቸው ፡፡

ጀርገን ክሎፕ ባርሴሎና የቁርጥ ቀን ልጃቸውን ፌሊፔ ኩቲንሆ ለመውሰድ መቃረቡን እና የብራዚላዊው ኮከብ ልብ መሻፈቱን ተከትሎ የዌስት ሀሙን ማኑዌል ላንዚኒ ለማዘዋወር ጥረት ጀምረዋል እንደ Mundo Deportivo ዘገባ።

የዌስት ሀሙ ኮከብ በአንፃራዊነት ከፌሊፔ ኩቲንሆ ጋር ተቀራራቢ ብቃት አለው ብለው ጀርመናዊው የጌጌም ብሬሲንግ አቀንቃኝ ጀርደን ክሎፕ ያምናሉ፡፡

አንቶኒዮ ኮንቴ ኔዘርላንዳዊውን ቨርጅል ቫን ዳይክ እና ሌሎች ተጨዋቾችን እንደሚያዘዋውሩላቸው ከቼልሲ የቦርድ አባላት ተስፋ ያደርጋሉ፡፡ (Source: The Mirror)

እንግሊዛዊው የስፐርስ አማካይ ኤሪክ ዳየር በባየርን ሙኒክ ራዳር ውስጥ የገባ ሲሆን የባቫሪያው ክለብ £50M አዘጋጅቷል ፡፡

ካሜሮን ቦሩዝ ዊክስ ጃክሰን ከአያክስ የቀረበለትን የዝውውር ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ነው ከማንቸስተር ዩናይትድ ወደ ሊድስ ዩናይትድ በረዥም ጊዜ የውሰት ውል የተዘዋወረው፡፡ (Source: ESPN)

ባርሴሎና የሊቨርፑሉን እና ብራዚላዊውን አማካይ ፌሊፔ ኩቲንሆ ዝውውር ለማገባደድ ከጫፍ ደርሷል (Source: Esporte Interativo)

ኒስ ሆላንዳዊውን ዌስሊ ሽናይደር በነፃ ዝውውር ለማስፈረም መስማማቱን ይፋ አድርጓል ፡፡ (Source: ogcnice )

ቼልሲ ሊቨርፑልን በሳውዝሀምተኑ ኔዘርላንዳዊ ቨርጅል ቫን ዳይክ ዝውውር ሊያሸንፈው ነው፡፡ ኒስ ሆላንዳዊውን ዌስሊ ሽናይደር በነፃ ዝውውር
ለማስፈረም መስማማቱን ይፋ አድርጓል ፡፡ (Source: ogcnice )

ቼልሲ ሊቨርፑልን በሳውዝሀምተኑ ኔዘርላንዳዊ ቨርጅል ቫን ዳይክ ዝውውር ሊያሸንፈው ነው፡፡ (Source: Sunday Mirror)

ምንጭ፡ አሪፍስፖርት

Leave a Comment