ጋቦን 2017:-አይቮሪኮስት ማሸነፍ ከብዷታል

ጋቦን 2017-አይቮሪኮስት

ከተጀመረ ሳምንቱን ነገ የሚደፍነው የ 2017 የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታዎች እየተካሄዱ ይገኛሉ።

ዲ ኮንኮ፣አይቮሪኮስት፣ቶጎ እና ሞሮኮ በሚገኙበት የምድብ 3 ሁለተኛ ጨዋታዎች ምሽት ላይ ሲካሄዱ ዝሆኖቹ ከ ነብሮቹ ጋር 2-2 ተለያይተዋል።

3 ጎሎች በታዩበት የመጀመሪያው ግማሽ ጨዋታ ዲ ኮንጎ በካባኖ የግማሽ ቮሊ ጎል አማካኝነት ቀዳሚ መሆን ቢችሉም ዊልፍሬድ ቦኒ አይቮሪኮስትን አቻ አድርጓል።

ጋቦን 2017:-አይቮሪኮስት ማሸነፍ ከብዷታል

ነገርግን “ነብሮቹ” ተመልሰው መሪ ለመሆን የደቂቃዎች እድሜ ብቻ አስፈልጓቸዋል።

ካባናንጋ ከቀኝ መስመር የተሻገረለትን ኳስ በአስደናቂ የግንባር ኳስ በድጋሚ ነብሮቹን መሪ አድርጎ ለእረፍት ወደ መልበሻ ቤት አምርተዋል።

ከእረፍት መልስ “ዝሆኖቹ” ተሽለው የተገኙበት ክፍለ ጊዜ ቢሆንም ኮንጎዎች ጨዋታውን ለመግደል አጋጣሚ ቢያገኙም አልተጠቀሙበትም።

ጫና ፈጥረው ሲጫወቱ የነበሩት አይቮሪኮስቶች 67ኛ ደቂቃ ላይ ሴሪ ዲ መሬት ለመሬት አክርሮ የመታው ኳስ ወደ ጎል ተቀይሮ በድጋሚ አቻ መሆን ችለዋል።

ጨዋታውን ለማሸነፍ የተሻለ ፍላጎት የነበራቸው አይቮሪኮስቶች አሸናፊ ሊያደርጋቸው የሚችለው ኳስ አቻ ከሆኑ በኋላም ቢያገኙ መጠቀም አልቻሉም።

ጨዋታውም 2-2 ሊጠናቀቅ ችሏል።በዚህም መሰረት ዲ ኮንጎ 4 ነጥብ ላይ ስትደርስ አይቮሪኮስት 2 ነጥብ ላይ ተቀምጣ ከምድቡ ለማለፍ የመጨረሻው ጨዋታ ከሞሮኮ ጋር የምታደርገውን ጨዋታ ትጠብቃለች።
ኢትዮአዲስ ስፖርት -በእዮብ ዳዲ

Leave a Comment