View Post

የኦሮሚያ ክልል አዳዲስ ሹመቶችን ሰጠ

View Post

የክልሉ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ በይፋዊ የፌስ ቡክ ገጻቸው እንዳሳወቁት፣ ሹመቶቹ የክልሉን የማስፈጸም አቅም ያሳድጋል ተብሏል፡፡ በዚህም መሠረት የተሰጡት አዳዲስ ሹመቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡

View Post

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዱባይና በቻይና የተከማቸ የውጭ ምንዛሪ እንዲመለስ ጠየቁ

View Post

የአገሪቱ ከፍተኛ ችግር እየሆነ ያለውን የውጭ ምንዛሪ እጥረት ለማርገብ መንግሥት ከሚወስዳቸው ዕርምጃዎች በተጨማሪ፣ ባለሀብቶችም በዱባይና በቻይና ያከማቹትን እንዲመልሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የንግድ ኅብረተሰቡን አሳሰቡ፡፡  

View Post

የግል አቪዬሽን ኩባንያዎች ተሽከርካሪዎቻቸው የአሥር ሚሊዮን ዶላር መድን እንዲገቡ መጠየቃቸውን ተቃወሙ

View Post

የዘጠኝ ወራት የዘርፉን አፈጻጸም ለመምከር የትራንስፖርት ሚኒስቴር በጠራው ስብሰባ ላይ የግል አቪዬሽን ኦፕሬተሮች ያደረባቸውን ቅሬታ አሰሙ፡፡ አውሮፕላኖች በሚንቀሳቀሱበት ወይም በምድረ አየር ክልል (በበረራ መነሻና ማረፊያ) ውስጥ ለሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች፣ የአሥር ሚሊዮን ዶላር የመድን ሽፋን ግቡ መባላቸውን ተቃውመዋል፡፡ የትራንስፖርት ሚኒስትር ዴኤታዎች በቀረበው ቅሬታ ላይ እንደሚነጋገሩበት አስታውቀዋል፡፡

View Post

ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የ45 ነጋዴዎችን የባንክ ሒሳብ ማገዱ ተቃውሞ አስነሳ

View Post

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በንግድና ኢንቨስትመንት የተሰማሩ 45 ኩባንያዎች በ18 ባንኮች የሚያንቀሳቀሱትን ሒሳብ በሙሉ ማገዱ ተቃውሞ አስነሳ፡፡ ባለሥልጣኑ የባንክ ሒሳባቸውን ያገደው ሕግን ባልተከተለ መንገድ መሆኑን የገለጹ ኩባንያዎች ጉዳዩን ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መውሰዳቸውን ተናግረዋል፡፡

View Post

ሜቴክ ለደን መመንጠሪያ የተከፈለው 2 ቢሊዮን ብር ጠፍቶበታል

View Post

ዋዜማ ራዲዮ- የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የሕዳሴው ግድቡ ዉሀ የሚተኛበትን ሰፊ ቦታ ከደን ነጻ እንዲያደርግ 2 ቢሊዮን ብር ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኮርፖሬሽን የተሰጠው ከዓመታት በፊት ነበር፡፡ አሁን ግን ገንዘቡ ሳይባክንብኝ አልቀረም እያለ ነው፡፡ ይህ ገንዘብ የተከፈለው ከመንግሥት አሠራር ውጭ ፣ ያለምንም መደበኛ ውል፣ ሥራው ተሠርቶ እንደተፈጸመ ተደርጎ መቶ እጅ ክፍያን በመፈጸም ነው፡፡

View Post

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሳምንት ክራሞት

View Post

ከተመረጡ ሁለት ሳምንታት ያስቆጠሩት አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ሥልጣናቸውን በተረከቡ በቀናት ውስጥ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሥራ ጉብኝት በማድረግ፣ ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር በመገናኘት ውይይት እያደረጉ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፈቃዳቸው ሥልጣናቸውን የለቀቁትን አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝን ተክተው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ከተሰየሙ በኋላ፣ ተከታታይ ሁለት ሳምንታትን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎችን የማነጋገር መርሐ ግብር ይዘው የሥራ ጉብኝቶችን ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡

View Post

ጠ/ሚ አብይ አህመድ በወልቃይት ጉዳይ ስለተናገሩት ከጎንደር ክ/ሃገር የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ህዝብ የአማራ ብሄርተኝነት የማንነት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴ በሰሜን አሜሪካ የተሰጠ መግለጫ

View Post

“ትልቁ ችግር የዲያስፖራው የኢንፎርሜሽን ምንጭ ፌስቡክ፣ሶሻል ሚዲያ ነው፡፡ ከዛ ይሰማና እውነት ያለቅን መስሎት፣የተባላን ስሎት፣ በዛ ስቃይ ውስጥ በአገኘው አጋጣሚ ሰላም ማውረድ ሳይሆን ነዳጅ መጨመር ይሆናል ስራው። ያ እንዲቀር እኔ ምመኘው ወልቃይት አከባቢ አርማጭሆ አከባቢ በዛም በዚህም ያሉት ዲያስፖራዎች ወደ አገራቸው መጥተው እንዲያዩት ህዝቡን፣የህዝቡን ኑሮ እንዲያዩት፣የህዝቡን ችግር እንዲያዩት። ህዝቡ እያለ ያለው ትምህርት ቤት፣ጤና ጣቢያ፣መንገድ፣መብራት ነው። ከዚህ ውጭ ያለው አጀንዳ የህዝብ አጀንዳ አለመሆኑን ሲያውቁ ብዙዎቹ ሳያውቁ ሚደናገሩት ከህዝብ ጋር ይሆናሉ የሚል እምነት አለኝ።

View Post

ፓርላማው የዘንድሮን ምርጫ ያራዘመበት ሒደት የሕጋዊነት ጥያቄ አስነሳ

View Post

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዘንድሮ መካሄድ የነበረበትን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተሞች ምክር ቤትና የአካባቢ ምርጫን ያራዘመበት መንገድ የሕጋዊነት ጥያቄ አስነሳ፡፡ ምክር ቤቱ ሐሙስ ሚያዝያ 4 ቀን 2010 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ፣ ዘንድሮ መካሄድ የነበረበት ምርጫ ለ2011 ዓ.ም. እንዲሸጋገር በስምንት ድምፀ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምፅ ወስኗል፡፡

View Post

ታዋቂው ብራዚላዊ አግርኳስ ተጫዋች ሮናልዲኒዮ ኢትዮጵያ ገባ።

View Post

ሮናልዶ ደ አሲስ ጋውቾ፤ በተለምዶ ሮናልዲኒዮ በመባል የሚታወቀው ብራዚላዊ እውቅ የእግር ኳስ ተጫዋች ዛሬ ረፋዱ ላይ ኢትዮጵያ ለጉብኝት ገብቷል። ሮናልዶ በ አዲስ አበባ ስታዲየም በመገኘት ከህዝብ ጋር እንደሚገናኝ ታውቋል። ሮናልዶ ከእግርኳሱ በተጨማሪ የዲጄነት ሞያው ያለው ሲሆን፣ ይህንኑ ሞያውን ተጠቅሞ ህዝቡን ለማዝናናት እንደተዘጋጀም ተነግሯል። ታዋቂው ብራዚላዊ አግርኳስ ተጫዋች ሮናልዲኒዮ ኢትዮጵያ ገባ።

View Post

የጠ/ሚ አብይ አህመድ የመጀመሪያ የውጭ ጉብኝት አስመራ ቢሆን መልካም ነው:: | ሃይሌና ልደቱ

View Post

ሻለቃ ሃይሌ ገብረስላሴ እና አቶ ልደቱ አያለው በጋራ በሰጡት ቃለመጠይቅ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የመጀመሪያ የውጪ ጉብኝታቸው ኤርትራ መሆን አለበት ብለዋል። ለዚህም አባባላቸው የየራሳቸውን ምክኛት ሲደረድሩ የሚከተሉትን ምክኛቶች በዝርዝር አስቀምጠዋል። የጠ/ሚ አብይ አህመድ የመጀመሪያ የውጭ ጉብኝት አስመራ ቢሆን መልካም ነው፣ ሃይሌና ልደቱ.

View Post

አንዳንድ ስለጤናችን በዶ/ር አቤል ጆሴፍ | ልብ ድካም [መነበብ ያለበት]

View Post

አንዴ አበሾች ከበዉ የአሜሪካን ኳስ (American football) ጨዋታ ሲያዩ ቆይተዉ ከተለያዩ በህዋላ አንዱ ግዋደኛቸው ከተኛበት ሞቶ ተገኘ፤ ይህም በሆነ ጊዜ ሁሉም በድንጓጤ ትላንት ከኛ ጋር ነበር፤ ሲዝናና ሲጫወት እንደነበርና ምንም አይነት የህመም ስሜት እንዳለነበረዉ ነገሩን።
ይሁንና ሰዉየዉ ወደ ስልሳወቹ የተቃረበ፤ ምንም የንት ህምም ያልነበረበት ነበር።
ከዶክተር ሂዶም ስለማያዉቅ ቢኖርበትም የሚነግረዉ የለም።
በኛ ባህል ሰዉ ወደ ዶክተር የሚሄደዉ ከተመመ ብቻ እንደሆነ ነዉ የሚታወቀዉ፤ እንደ ምእራቡ አለም በ አመትም ሆነ በስድስት ወር ለቸክ አፕ ብሎ መሄድ የሚባል ነገር የለም።

View Post

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከምሬትና ቁዘማ ወጥተው በአዲስ መንፈስ ሊሰሩ እንደሚገባቸው ገለፁ | ፋና ብሮድካስቲንግ

View Post

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለህዝቡ አማራጭ ሆኖ ለመገኘት ለሚያደርጉት ጥረት ምስጋና አቀረቡ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በብሄራዊ ቤተመንግስት ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች ጋር ለእራት ተቀምጠዋል። በዚሁ ስነ ስርዓት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተፎካካሪ  የፖለቲካ ፓርቲዎችከምሬትና ከቁዘማ ወጥተው በአዲስ መንፈስ ለለውጥ ሊሰሩ እንደሚገባ ገልጸዋል ። ማንኛውም አካል በሰላማዊ መንገድ መደራደር የሚፈልግ ካለ ኢህአዴግ …

View Post

Ethiopia : Breaking | አቶ ለማ መገርሳ ስለ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ

View Post

ይህ የኢትዮጵያዊነት ስሜት በአቶ ለማ እና ዶ/ር ዓብይ በእራሱ በህወሓት መንደር ውስጥ ተስተጋብቶ ባለፈው ቅዳሜ ጅጅጋ ላይ ተደግሟል።የኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል ዋና ከተማ ጅጅጋ እና የአካባቢው ነዋሪ ከፍተኛ ባለስልጣን ወጥቶ ለመቀበል አደባባይ የወጣው ምናልባት ከኮለኔል መንግስቱ ዘመን ወዲህ ለመጀመርያ ጊዜ ባለፈው ቅዳሜ መጋቢት 29/2010 ዓም ነው።