View Post

የካቢኔው ሹመት (አፈንዲ ሙጠቂ)

View Post

ለምሳሌ አህመድ ሺዴን ከመሾምና አቶ ክቡር ገናን ከመሾም የቱ ይበልጣል? ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊን ከመሾምና ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚልን ከመሾም የቱ ይበልጣል? ከአቶ አብዱ ዐሊ ሂጅራ እና ሀቃቤ ህግ ነኝ ከሚለው ሰውዬ በችሎታ፣ በእውቀትና በልምድ የቱ ይበልጣል?

View Post

አቶ ለማ የመጠናከሪያ ሹም ሽር ሲያደርጉ፤ ዶ/ር አቢይ ደግሞ ድጋፍ ወይም ተቃውሞ የሚያስነሳ ሹም ሽር ለማድረግ ይጠበቃሉ- (ወንድወሰን ተክሉ)

View Post

አቶ ለማ መገርሳ የቲም ለማ ቡድንን ያጠናከረ የተባለለትን የሹም ሽር ውሳኔ እረቡእ እለት አድርገዋል፡፡ በውሳኔያቸውም 20ባለስልጣናትን ሽረው የሾሙ ሲሆን አራት የሚሆኑ የፌዴራል ምኒስትሮችንም ወደ ክልሉ በማዛወር ሾመዋል፡፡

View Post

ወልቃይት ጉዳይ የመላው አማራ ጉዳይ ነው! (ሊዲያ ዘ-ጊዮን አማራ)

View Post

የወልቃይት እና መሰል ስፍራዎች ጉዳይ ለሃሳዊ ኢትዮጵያኒስቶች አንግዳ ህሳቤ ነው፤ አውቀነዋል ብለው እንኳ ብዙዎች በወልቃይት ጉዳይ ላይ ሲወዛገቡ ይስተዋላሉ። ለምሳሌ ከሰአታት በፊት ኢሳት (ኦሳት) ላይ በወልቃይት ጉዳይ ላይ ሲሳይ ኣጌና ሲያብራራ ስሰማው ችግሩን በገርፍ ነው የሚያውቀው። ይህንን ስል ፀረ-አማራ ስልታቸውን የሚዘውሩባት ረቂቋ ሸር ባሻገር የተገነዘብኩት ነገር ስላለ ነው:: በሙሉ ተወያዩ በወልቃይት ጉዳይ ላይ ያለውን የህግም አተገባበር አያውቁም። ብቻ ያን ሰሞን በአማራው ደንደስ. ግምቦት -1 ተወደስ ለማድረግ ደፋ ቀና ሲሉ በነበረበት ወቅት ተጋድሎ በፈነዳ ሰሞን ለራሳቸው ፍጆታ ሽፋን መስተጠት በተገደዱ ግዜ ቆንጽለው በወሰዷት ህሳቤ ላይ ብቻ እስከ አሁን ድረስ ቸክለው ይነባነባሉ።

View Post

ባለፉት 27 ዓመታት የትግራይ ተወላጆች የያዙትን የፖለቲካ አቋምና ምክንያቶቹ (ወልደአብ ድንቡ )

View Post

ይህ ጽሁፍ ባለፉት 25 ዓመታት የትግራይ ……………………….በሚል እ.ኤ.አ በ16/12/2016 ለአንባቢያን አደባባይ ወጥቷል። ዶ/አብይ ለጠቅላይ ምኒስተርነት መመረጥ ዋዜማ ድረስ ፤ “በኢትዮጵያ የበላይነት የነገሠው ትግራይዊነት ወይስ ህወሃታዊነት” በሚል በተለያዩ ሚዲያ ዘርፎች ለአራት ሳምንታት ያህል የጦፈ ክርክር (boiling dispute) በመደረግ ላይ እያለ አሸናፊውና ተሸናፊውን ሳይታወቅ ወደ ዶ/አብይ ሹመት አውንታዊና አሉታዊ ፋይዳ ታይታና  ክርክር ተዞረ/ተገባ። <1> በዚህ ጽሐፍ ላይ አንዳንድ ተዛማጅ ነጥቦች ስለታከለበት <2> ህወሃት/ወያኔ ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሕዝብ እስከገዛ እና ትግሬዎች ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን ተሰልፈው የህወሃት/ወያኔ ግፍ እስካልተቃወሙ ክርክሩን መቀጠሉን ስለማይቀር፤ ይህ ጽሁፍ ለክርክሩ አስተዋጾ ያደርግ ይሆናል ብለን በማሰብ አደባባ እንዲወጣ ፈለግን ።

View Post

ፋታ ለማን? (ዶ/ር ዘላለም እሸቴ)

View Post

በጃንሆይ ዘመነ መንግስት ልጅ እንዳልካቸው መኮንን ፋታ ስጡኝ እያሉ ቢጣሩም፥ ሰሚ አጥተው አቶ ጥድፊያ ኢትዮጵያን ላለፉት ዓመታት ለመከራ አሳልፎ እንደሰጣት እናውቃለን። ከታሪክ ጠባሳ ካልተማርን ታሪክ ራሱን ይደግማል። ለዶ/ር አብይ አህመድ ፋታ እንዲሰጥ የሚያስፈልገው ለእርሳቸው ስልጣን ማራዘሚያ አይደለም። ፋታ የምትፈልገው ኢትዮጵያ ናት። አሁንም ዶ/ር አብይን የሚያዋክቡ ወገኖቻችን ዓይናቸውን ከእሳቸው ላይ አንስተው እናት ሀገር የምትባለው ኢትዮጵያ ያለችበትን ምጥ ማየት ቢችሉ መልካም ነው። ጊዜው አዲሲቷ ኢትዮጵያ ለመወለድ ጫፍ ላይ ያለችበት ወቅት ይሆን ይሆንን? በማለት የአዋላጅነት ሚና እንድንጫወት ሁላችንም መጣር ያለብን ወቅት ነው። ከጥንቃቄ አንጉደል።

View Post

ዶ/ር አብይን ለቀቅ፣ ወገብን ጠበቅከ (ያሬድ ኃይለማርያም)

View Post

የጠ/ሚ ሹመታቸውን ከያዙ ወር እንኳ ያልሞላቸው ዶ/ር አብይ አስገራሚ የሆነ ሕዝባዊ ድጋፍ ባገኙ ማግስት በተደጋጋሚ፤ በተለይም በመቀሌ ባደርጉት ንግግር ተቃውሞን እያስተናገዱ ነው። በፓርላማ ባደረጉት ንግግር እጅግ ደስ ከተሰኙትና ተስፋም ከሰነቁት ሰዎች መካከል አንዱ እኔ ነኝ። ደስታዮ አሁንም እንዳለ ነው።

View Post

መከዳቴ በጀኝ እንዳይህ አድረገኝ (ሊዲያ ዝ-ጊዮን አማራ)

View Post

የጀርመን ጦር በርቶት ከሞስኮ በመቶ ማይሎች ርቀት ላይ ይገኛል:: ራሻ በድንጋጤ እንደተመታና ኮማ እንደገባ ነው:: ስታሊን በሂትለር መከዳቱን ማመን አቅቶት ቆራጥ የጦር ውሳኔ መስጠት እስኪያቅተው ድረስ ድንጋጤ ቤቱን ሰርቶበታል:: ጀርመን-ራሺያ Non-Aggression Pact ፈርመው አንዳቸው አንዳቸውን ላይወጉ ተማምለው ሳለ መኃላ አፍርሶ ቃል አጥፍቶ ሂትለር ጦር መስበቁ ስታሊንን በድንፋጤ በረዶ አድርቆት ቀዝቅዟል:: ጀርመን ጦር ብዙ በሺህ የሚቆጠሩ ራሻዎችን በላ:: አንድ ነጥብ አምስት ሚሊየን ራሺያ ዘብ እስረኛ ተደርጎ ተማረከ:: ኪቭ ላይ ቀዩ ጦር ቀይ ደሙን ገበረ:: የጀርመን ናዚ ስልታዊነት ራሻን ያንን የጀግና አገር አንዘፈዘፈ:: እነ Belorussia, እነ Ukraine እነ Baltiን ጀርመን በቁጥጥሯ ስር አደረገች::

View Post

በኢትዮጵያ ሁለት መንግስታት አሉ | የውሸት መንግስትና የስውር መንግስት። (ዶ/ር ብርሃነመስቀል አበበ ሰኚ)

View Post

የውሸት መንግስቱ አለማ የኢትዮጵያ ህዝብን በመደለል የህወሃትን የፓለቲካና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት መረጋገጥ ነው። የስውር መንግስቱ አለማ የውሸት መንግስቱን መዋቅሮችና ፓሊሲዎች ለህወሃትና ተባባሪዎቻቸው የኢኮኖሚና የፓለቲካ የበላይነት መስራት ነው።

View Post

ርስት ለባለቤቱ (ሊዲያ ዘጊዮን አማራ)

View Post

በእውነቱ ከሆነ እስከ አሁን ወያኔ በአደገኛ ሁኔታ machiavellianism style ተጥቅማ ፖለቲካውን ለማጣጠፍና በፖለቲካ ምህዳር የበላይነትን መያዝ ችላ ነበር:: ነበር። ነገር ግን የሾመችው ሰው ስልጣን በያዘ በ፩፫ኛ ቀን ላይ ካርዷን በሙሉ አቃጥሎ ጨርሶባታል፤ ይሄንን የደረሰባቸውን ያልታሰበና ያልተገመተ ነው ብል የምሳሳት አይመስለኝም። በተናገረ ቁጥር አየፎረሸባቸው ተቸግረው የድህረገጽ ጸሀፍቶቻቸው በdamage control ስራ ላይ ተጠምደው ይስተዋላሉ።

View Post

የአብይ አቋምና የሚያመጣውስ ለውጥ ምንድን ነው? (ወረታው ዋሴ )

View Post

ዶ.ር አብይ አምቦ ላይ ባደረገው ንግግር “ለዚህ ድል የበቃነው (ጠቅላይ ሚንስትር ለመሆን ማለቱ ነው) በእናንተ (በቄሮ) ተጋድሎና መስዋዕትነት በመሆኑ ምስጋናየን አቀርባለሁ” ብሏል። ይህ ማለት የሕወሃትን የበላይነት አሽቀንጥረን በመጣል በኦህዴድ መሪነት የተካነው እንደ ድርጅትም (ኦህዴድ) ይሁን እንደ ህዝብ (ቄሮ) በትብብር ባደረግነው ትግል ነው ማለት ነው።

View Post

ቤተመንግሥት እራት የበላቹህ ምን አተረፋቹህ? (ኤርሚያስ ቶኩማ)

View Post

አሁን ላይ ደግሞ የአዲሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ሹመት ምክንያት በማድረግ በቤተመንግሥት በተዘጋጀ የእራት ግብዣ የተወሰኑ ፖለቲከኞች እና አርቲስቶች ተሳትፈው የነበረ ሲሆን በእራት ግብዣው ላይ በመገኘታቸው ምን እንዳተረፉ እና የእነርሱ እዛ መገኘት በሕዝቡ ነፃነት ትግል ላይ ምን እሴት እንደሚጨምር ቢነግሩን ደስ ይለኛል።

View Post

ከዚህ ከአቶ ምላሱ ንግግር የተረዳሁት ሁለት ዋና ነገር ልጠቅስ:: ለወያኔ ሁለት እራስ ምታት ሆኖ የሚቀጥል ነገር አለ:: (ሊዲያ ዘ-ጊዮን አማራ)

View Post

የወልቃይትን ጉዳይ አብይ አድበስብሶ እንዲያልፍና ችግሩ የውሀ የዳቦ ማስመሰል እንዲያልፍ በተሰጠው ትእዛዝ መሰረት በጣረበት በዚህ ንግግር ወያኔ የረባ መላ መምታት እንዳልቻለች ያሳያል:: የአማታው ትግል ትኩሳቱ እንደሚጨምርም አመላካች ነው:: አንፃራዊ መረጋጋትን ፈጥሮ ብድር እንዲለቀቅለት ከፈለገ ወያኔ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ወልቃት መተከል (ቤኒሻንጉል የተባለ መለስ ሰራሽ ክልል ሙሉ በሙሉ ማፍረስ ግድ ይለዋል) ራያን ባስቸኳይ መመለስ ግድ ይለዋል::

View Post

ዶ/ር አብይ አህመድ መፍትሄ ወይስ ችግር? (ስዩም አርጋው)

View Post

ዶ/ር አብይ አህመድ የበግ ለምድ የለበሰ ተኩላ መሆኑን በመቀሌ ስብሰባ ላይ ስለ ወልቃይት ህዝብ የማንነት ጥያቄና ዲያስፖራ የተናገረውን ማንነቱን ያሳየ ይመስለኛል። ዶ/ር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን የመጣበት ምክንያት ገና በ12 ቀናት ውስጥ የረሳው ይመስለኛል። ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ያለው የህዝብ ቁጣ መንስኤው ለረጅም ጊዜ የቆየ ቢሆንም በዚህ ደረጃ ገዝፎ ትግሉ እንዲቀጣጠል ያደረጉት የእስልምና እምነት ተከታዮች የእምነት ነፃነት ጥያቄ፤ የአዲስ አበባ አዲሱ ማስተር ፕላን፤ የወልቃይት ህዝብ የማንነት ጥያቄ፤ የጉራጌ የጤና፣ ትምህርትና የግብርና ምርምር ተቋም መታጠፍ ከብዙዎቹ ዋናዋና ተጠቃሽ ናቸው።

View Post

በዚሁ ከቀጠለ ወያኔ/ኢህአዴግ በህይወት ሊቆይ የሚችለው የዶ/ር አብይ ንግግሮች እስኪያልቁ ድረስ ብቻ ነው!

View Post

በነበረው መቀጠል በራሱ “አልሸሹም ዞር አሉ…” የሚባለውን ድራማ እያቀላጠፉ፤ “ላም አለኝ በሰማይ…” ተስፋዎችን እየመገቡ፤ ሊቀጥሉ ረጅም ግብ ነድፈው እየተንቀሳቀሱ ነው ማለት ነው። ያም ሆነ ይህ የኢትዮጵያ ህዝብ ወያኔ/ኢህአዴግ ያረጀ የበሰበሰና የተቦረቦረ ባዶ ድርጅት እንደሆነ በሚገባ ያውቃል፤ አገር መምራትም የሚችልበት አቅም እንደሌለውም ጭምር።

View Post

የምንመኘውን እናገኝ ይሆን? (ባይሳ ዋቅ-ወያ)

View Post

የዶ/ር ዓቢይን መሾም አስመልክቶ ብዙዎቻችን የተሰማንን ስሜት ከያቅጣጫው አሰምተን ነበር፣ ዛሬም እያሰማን ነው። የሚሰነዘሩትን አስተያየቶችና የድጋፍ ወይም የተቃውሞ ድምጾችን በሚከተሉት አራት ክፍሎች መድቤያቸዋለሁ። የመጀመርያው ቡድን የዶ/ር ዓቢይን መመረጥ ለኢትዮጵያ ትልቅ እፎይታ ነው፣ ሰላምና መረጋጋትን ብሎም ዲሞክራሲና እኩልነትን ያሰፍንልናል፣ እግዜር እንደ ሙሴ ከምድረ በዳ አውጥቶ ወደ ተስፋዋ ምድር ሊመራን በትሩ ተሰጥቷቸዋል በማለት መቶ በመቶ እምነታቸውን የጣሉባቸው ነው። ሁለተኛው ቡድን ደግሞ ከዚህ በጣም ተቃራኒ የሆነና ዶ/ር ዓቢይ ሥርዓቱ ኮትኩቶ ያሳደጋቸውና ሥርዓቱ ደግሞ በኢትዮጵያውያን ላይ ያደርስ የነበረውን ግፍ ከውስጥ ሆነው በዕቅዱም በአፈጻፀሙም ላይ ተካፋይ የነበሩ ግለሰብ ስለሆኑ አንዳችም ዓይነት ለውጥ ሊያመጡ አይችሉም፣ እንዲያውም ኢህአዴግ አሁን ያጋጠመውን ውጥረት ለማስተንፈስ ለጊዜው መፈናፈኛ እንዲሆን ወያኔ  ሆን ብላ ህዝቡን ለማወናበድ ያደረገችው የፖሊቲካ ጁዶ ነው እንጂ ለህዝቡ አንዳችም ዓይነት ለውጥ ሊመጣ አይችልም ይላሉ።